Pages

Saturday, February 27, 2010

First Ethiopian & Black African jet pilot

ካፒቴን አለማየሁ አበበ (Captain Alemayehu Abebe)

abe

ኬንያ ተልኬ ጥቂት በረራዎች ካደረግሁ በኋላ በፌብርዋሪ መጨረሻ 1963 ዓ.ም በኢትዮጵያ አየር መንገድ የጄት ካፕቴንነቴ ተሰጠኝ፡፡

የአብራሪነት ኃላፊነቱን ከተረከብኩ በኋላ አንዳንድ መንገደኞች አብራሪው ነጭ ባለመሆኑ ከሚያሳዩት መደናገጥ በቀር ምንም እንከን ሳያጋጥመኝ አየር መንገዱ በሚገለገልባቸው አፍሪካና አውሮፓ መብረር ጀመርኩ፡፡ በስልሳዎቹ አሥርተ ዓመታት መጀመሪያ ላይ አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች ከቅኝ ገዥዎች ቀንበር ነጻ ለመውጣት የሚታገሉበት ወቅት ስለነበር ጥቁር ፓይለት በሚያበረው ዘመናዊ ጄት ለመሳፈር እንኳን ለባዕዳን ለወገኖቻችንም ቢሆን መደናገጥን ፈጥሮ ነበር፡፡ ይኸው የመጀመሪያ ዓለም አቀፍ በረራ አብቅቶ መሬት እንዳረፍን መንገደኞቹ ሲሰናበቱን ከልብ የመነጨ ምሥጋና ያቀርቡልን ነበር፡፡ አንዳንዶች ኢትዮጵያውያንማ ማመኑም እየቸገራቸው ሳይሆን አይቀርም በአድናቆት ይመለከቱንና ያነጋግሩን ነበር፡፡ በተከታታይ በረራዎች የመንገደኞቼ ሥጋትና ጥርጣሬ ወደ መተማመን ተለውጦ ባየሁትና በሰማሁት ቁጥር የሥራ ባልደረቦቼም ሆኑ እኔ ደስታ ይሰማን ነበር፡፡ በሥራ ውጤት እምነት ከማግኘት የበለጠ ምን ነገር ይኖራል”

እርግጥ ነው ስንት ፈተና በትዕግሥት አልፌ ለዚያ ደረጃ እንደበቃሁ መንገደኞቼ አያውቁም ነበር፡፡ ቢያውቁስ ኑሮ “አፍሪካዊ ጄት ሲያበር ለመጀመሪያ ጊዜ በማየታችሁ ለምን ትፈራላችሁ ለምንስ ትጠራጠራላችሁ?” ብሎ መጠየቅስ ይቻል ነበር? በእኔ ላይ የደረሰው ዓይነት በተከታዮቹ አብራሪዎች ላይም ደርሶ እነርሱም በትዕግሥትና በፅናት አልፈውታል፡፡

(ካፕቴን ዓለማየሁ አበበ፣ ሕይወቴ በምድርና በአየር፣1997)

No comments:

Post a Comment